Amharic

img 6393

የኢትዮጵያ ጠጅ

በኒው ጀርዚ የተመሠረተ የጠጅ/ሜድ አምራች፣ ባህላዊና ዘመናዊ ጠጆች ላይ የሚሰራ፣ ከአካባቢ የተሰበሰበ ማር በመጠቀም በትንሽ መጠን የሚፈላቀል እጅ ሙያ ሥራ የተደረገው።


standalone mockup classic mead 2

ታሪካችን

ቢቶፒያ (Beetopia) በኒው ጀርዚ የተቋቋመ የተወሰነና የጠራ የጠጅ ምርት የሚሰራ ፉብሪካ ነው።  የተለያዩ ቃና ያላቸው ጠጆች በተወሰነ ቁጥር ያመርታል። በዓለም ላይ ጥንታዊና ከተከበሩ መጠጦች አንዱ የሆነውን ጠጅ/ሜድ እንደገና ለማስተዋወቅ የተቋቋመ ድርጅት ነው። የምንጠቀምበት ማር በጥንቃቄ የተመረጠና ከፍተኛ ጥራት ያለው ነው።  ይህ ማር ከንጹሕና ከተጣራ ውሃ ጋር በጥንቃቄ ከተመረጡ የእርሾ ዝርያዎች ጋር በማጣመር ባህላዊነቱን ጠብቆ በዘመናዊ የእጅ ሙያ የተዘጋጀ ነው።

ጠመቃ

የጠጅ ጠመቃ ትዕግስት፣ በቂ ጊዜና ጥንቃቄ የሚጠይቅ ሥራ ነው። እያንዳንዱ የጠጅ አይነትና ምርት በጥንቃቄ ይጠመቃል። ይህም ማለት ፣ እያንዳንዱ የጠጅ አይነት፣ የማዘጋጃው ጊዜ፣ ያለው መዓዛና ጣዕም፣ ከብዙ ሙከራና ጥናት በኃላ የተገኘ ውጤት ነው።  ጠጆቻችን፣ ንጹሕና የተለያዩ ጥሩ የአበባ ሽታ፣ የሎሚ፣ የቅማ ቅመም፣ የተለያዩ ፍሬዎች ጣዕም የያዘና ፣ ግሉተን የሌለው መጠጥ ነው። እያንዳንዱ ምርት፣ የተለያየ ጣፋጭነት፣ ጣዕምና ቃና አለው።

28caab6c e727 401d 9013 a0471c7d963e
standalone mockup blueberry blossom 2

ፍልስፍናችን

ጥንታዊ ባህሎችን መንሰኤ አድርገን ፣ ጊዜውን የጠበቀ፣ በሚሰማማ መልክ የተዘጋጀ ፣ ከደረቅ እስከ ጣፋጭ የጠጅ አይነቶች አቅርበናል። እያንዳንዱ ምርታችን ንቦቹ በተለያየ ወቅቶች ስለሚቀሰሙት አበቦች፣ ሰለሚሰጡት ማር እንዲሁም ሰለአሰራራቸው ታሪክ ይነግራል። ቢቶፒያ ፉብሪካ ፣ አምራቾች ብቻ  ሳንሆን፤ የታሪክ፣ የሙያና እና የተፈጥሮ ጠባቂዎች ነን። ሰለዚህ ይህን እሳቤ በማድረግ ፣ ባህላችንና ክብራችንን የጠበቀ መጠጥ ለማምረት በትጋት እንሰራለን።


ከእኛ ጋር ያግኙ

This field is required.

© 2025 Beetopia LLC. All rights reserved.

Cherry Hill, NJ, USA